የዐውድማ ትውፊት፣ ሃይማታዊና ማኅበራዊ ፋይዳ፤ የምርት ብክነት ምክንያቶቹ በጎጃም የአመራረት ሂደት
Research Paper
v አማኑኤል ይግረም (ኤም.ኤ. በጂ. እና አካባቢ ጥናት) - ዋና ተመራማሪ ረዳት ተመራማሪዎች፡- v ሊ.ኅ. ተግባሩ አዳነ (ሊቀ ኅሩያን፣ ኤም.ኤ. በፊሎሎጂ/ሥነ ልሳን) v ሃይማኖት አረጋኸኝ (ኤም.ኤስ ሲ. በግብርና ምጣኔ ሀብት) v ልቅናው ይርሳው (ፒኤች.ዲ. በሥነ ጽሑፍ) v ወንድአለ ተመስገን (ኤም.ኤስ ሲ. በሶስዮሎጂ) v ካሳሁን ውባለም (ኤም.ኤስ ሲ. GIS and Remote Sensing)
Submitted: Oct 06, 2025
Social Science and Humanities
Geography and Environmental Studies(GeES)
Abstract Preview:
ዐውድማ ሰብልን ለመውቃት ኣገልግሎት የሚውል በክብ ቅርጽ የሚዘጋጅ የራሱ የሆነ ሃይማኖታዊ ባህላዊ እና ኢኮኖሚያዊ ይትባህል ያለው በሃገራአችን ኢትዮጵያ ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ነው። የዐውድማ ተግባር የጾታ፣ የ እድሜ እና መሰል ነገሮች የማይለያዩት ሁሉም በህብረት የሚመለከተውን ድርሻ የሚወጣበት፣ እንስሳቱም አስተዋጽኦ የሚያደርጉበት የአርሶአደሩ የመጨረሻ ውጤት የሚታይበት፣ ገለባው ለንእስሳት መኖ የሚሰበሰብበት ክዋኔ ነው።የዚህ ምርምር ዋና አላማ ዐውድማ በጎጃም አርሶ አደሮች ዘንድ ያለውን ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ማህበራዊ ትውፊት በዐውዱ መተንተን፣ መሰነድ እና በሂደቱ ውስጥ የሚኖረውን የምርት ብክነት መንስኤዎችን መግለጽ ነው፡፡ ጥናቱ ያተኮረው በጤፍ፣ በስንዴና በገብስ ሰብሎች ላይ ነው። ጥናቱ በምሥራቅ ጎጃም ዞን መልክአ ምድሩን መሠረት አድርጎ በተመረጡ ወረዳዎች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡ እነዚህም በደጋ፣ ወይና ደጋ እና ቆላማ ቦታዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ የተመረጡ ናቸው፡፡ ጥናቱን የተሟላ ለማድረግ በፌኖሚኖሎጅ ዘዴ መረጃውን ከሚያውቁት ሰዎችና ከሚገኙበት ቦታ ድረስ በመሔድ በመስክ የቀጥታ ምልከታ ከቀዳማይ ምንጮች ለመሰብሰብ የሚያስችል ተጨባጭ የምርምር ዘዴ ነው፡፡ በመሆኑም በሃገራችን ኢትዮጵያ በተለይ በመረጥነው የምርምር ቦታ ዐውድማ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜት ያለው ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የራሱ የሆነ ስነቃሎች ያሉት ጠቃሚ ስርዓት ነው። ነገር ግን አሁን ስርዓቱ እየቀዘቀዘ መምጣቱን እና አብሮነት እና መተጋገዝ እየጠፋ አቅመደካሞች በጋራ(ከብት የሌለው በጉልበቱ) የሚለውን ይትብሃል እንዳይጎለብት፣ በዐውድማ ክዋኔ ወቅት የሚኖረውን የምርት ብክነት ብቻ በማየት ጠቀሜታውን በመዘንጋት ወደ ዘመናዊ ኮምባይነር የመቀየር ተግባር መኖሩን በመረጃ ማረጋገጥ ተችሏል። አሁን በሚኖረው ሁኔታ በዐውድማ ስርዓት የሚኖሩ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ኢኮኖሚያዊ ክዋኔዎች በዚሁ ከቀጠሉ የሚረሱ እና የሚኖረው እሴት የሚጠፋ መሆኑን ድምዳሜ ላይ መድረስ ይቻላል። በመሆኑም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገራት(የአርሶአደሩ የመሬት ጥበት፣ መልካምድሩ ገባ ወጣ ማለት፣የሰው ሃይል በብዛት ያለበት፣ለአቅመ ደካሞች የሚኖረውን ፋይዳ በመዘንጋት፣ የሰብሉ አደራረስ በተለያየ ጊዜ በሚደርስበት ወዘተ) ዐውድማ አስፈላአጊ ስርዓት በመሆኑ የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጠው ማመላከት እንወዳለን።
Full Abstract:

Restricted Access
Contact system administrators for access
Read Full Abstract